የሐራ ከተማ አስተዳደር የእውቅና፣ የምስጋና እና ገቢ ማሰባሰቢያ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው

 

የካቲት 22/2013 (ዋልታ) – ሐራ ከተማ ወደ ከተማ አስተዳደርነት ማደጓን ተከትሎ የእውቅና፣ የምስጋና እና ገቢ ማሰባሰቢያ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡

በ1900 ዓ.ም እንደተመሠረተች የሚነገርላት ከተማዋ ከወልድያ ከተማ በ20 ኪሎ ሜትር ርቀት በስተምስራቅ አቅጣጫ ትገኛለች፡፡

ከተማዋ የአማራ ክልል መንግሥት በቅርቡ ወደ ከተማ አስተዳደርነት እንዲያድጉ ከወሰነላቸው ከተሞች አንዷ ናት።

ሐራ የአዋሽ – ወልዲያ -ሐራ ገበያ የባቡር ጣቢያ የሚገነባባት ከተማ መሆኗን አብመድ ዘግቧል፡፡