ቢዮንሴ በግራሚ አዋርድ አዲስ ሪከርድ አስመዘገበች

ቢዮንሴ ኖውልስ

መጋቢት 06/2013 (ዋልታ) – ቢዮንሴ ኖውልስ በግራሚ አዋርድ ላይ ለ28ኛ ጊዜ በማሸነፍ  አዲስ ሪከርድ አስመዝግባለች።

በግራሚ ታሪክ ከፍተኛ ሽልማትን በመሰብሰብ ቢዮንሴ ቀዳሚ ሆናለች፡፡

በዚሁ የትላንትና ምሽት የግራሚ ሽልማት ታይለር ስዊፍት ታሪክ ፅፋለች፡፡ የመጀመሪያዋ ሴት አርቲስት ሶስት ጊዜ የምርጥ አልበም ሽልማትን መውሰድ ችላለች፡፡

ቢዮንስ በግራሚ አዋርድ ላይ ለጥቁሮች ክብር የሰራችው ዜማ አሸናፊ አድርጓታል፡፡

ይህ ስራ ከጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ጋር በተያያዘ “መተንፈስ አልቻልኩም” ከሚለው የመጨረሻ ቃሉ የተወሰደ ነው፡፡