ሬድፎክስ የተሰኘ የመረጃ ቋት ማዕከል ይፋ ሆነ

ዶክተር እዮብ ተካልኝ

መጋቢት 7/2013 (ዋልታ) – የዲጂታል ኢኮኖሚውን የሚያጠናክር ሬድፎክስ የተሰኘ የመረጃ ቋት ማዕከል ይፋ ሆነ፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ መረጃ አዲሱ ነዳጅ መሆኑን ገልጸው፣ የዲጂታል መሰረተ ልማቱ መጠናከር በጤና፣ በትምህርት፣ በግብርና እና በሌሎች መስኮች ላይ አስተዋጽኦን ያሳርፋል ብለዋል፡፡

ሬድፎክስ ለረጅም ዓመታት በቴሌኮም ዘርፍና በመረጃ ቴክኖሎጂ ልምድ ባካበቱ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች የተቋቋመ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ሚኒስትር ዲኤታው ዳያስፖራዎቸ በዘርፉ ላይ በመሰማራታቸው ያላቸውን አድናቆት መግለጻቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡