ኮርፖሬሽኑ ከኤች ኤንድ ኤም ተወካዮች ጋር በመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ዙሪያ ተወያየ

መጋቢት 10/2013 (ዋልታ) – የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ ከኤች ኤንድ ኤም ተወካዮች ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይቱ በመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ነበር ተብሏል፡፡

ሁለቱ ወገኖች ለዘርፉ እድገት እና የተቀመጡ ሁሉን አቀፍ የልማት ግቦችን ለማሳካት በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ከኮርፖሬሽኑ ያኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኤች ኤንድ ኤም በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪ ልማት ለኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ አጋር ነው፡፡