የአለም አዕምሮ እድገት ውስንነት ቀን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከበረ

መጋቢት 12/2013 (ዋልታ) – የአለም አዕምሮ እድገት ውስንነት (Down syndrome) ቀን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከበረ።

ቀኑን በማሰብም ከደንበል እስከ ዲቦራ ፋውንዴሽን የ1.2 ኪሎ ሜትር የእግር ጉዞ ተካሂዷል።

በመርኃግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራች አባዱላ ገመዳ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍና  ካደረግንላቸው ምንም ማድረግ ይችላሉ ብለዋል።

የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ የሚታይ የአካል ጉዳት ያለባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ለማድረግ የምንጥረውን ያህል የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ህፃናትን ትኩረት ልንሰጥ ይገባል ብለዋል።

የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርም የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

(በሱራፌል መንግስቴ)