በኮቪድ-19 ወቅታዊ ሁኔታና ዓመታዊ ሂደት ላይ ውይይት ተካሄደ

መጋቢት 13/2013 (ዋልታ) – የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ከሰዎች ለሰዎች እና ከኮቪድ-19 ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪዎች ጋር በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወቅታዊ ሁኔታና ዓመታዊ ሂደት ላይ የዳሰሳ ውይይት አካሄዱ።
በዌቢናር በተካሄደው ውይይት በአመት ውስጥ ኮቪድ-19ን ለመከላከል የተካሄዱ እንቅስቃሴዎችና ውጤታቸው ላይ ግምገማ የተካሄደ ሲሆን፣ ወደ ፊት መከናወን ስለሚገባቸው ጉዳዮች ተመልክቷል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ በመከላከል ሂደት ያጋጠሙ ወሳኝ ችግሮች ምን ነበሩ፣ ከነሱ የተወሰዱ ተሞክሮዎች ምንድን ናቸው በሚለውና የክትባት አሰጣጥ ሂደትን በተመለከተ በውይይቱ መዳሰሱን ዶክተር ሊያ አስታውቀዋል።
በውይይቱ አለም አቀፍ የዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች መሳተፋቸውም ተነግሯል።