ሀገር ወዳድ ዜጋን ለመፍጠር የኃይማኖት ተቋማት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

መጋቢት 13/2013 (ዋልታ) – የኃይማኖት ተቋማት ኃላፊነት የሚሰማውና ሀገር ወዳድ ዜጎችን ከመፍጠር አንፃር ያላቸውን ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ፡፡

“ሀገሩን የሚወድ ጀግና መፍጠር” ላይ  የቤተክርስቲያንን አበርክቶ አስመልክቶ አውደ ጥናት ተካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሀገሩን የሚወድና ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋን ለመፍጠር ታሰቦ በተዘጋጀው 4ኛው አውደ ጥናት ላይ ሁሉም ሰው ሀገሩን መውደድና ሀገሩን ማስቀደም ይጠበቅበታል ተብሏል፡፡

በተለይም ትውልድን ለመቅረፅና ሀገሩን የሚወድ ዜጋን ለመፍጠር የኃይማኖት ተቋማት ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተነስቷል፡፡

ኃይማኖቱን የሚወድ ሰው ሀገሩን መውደድ፣ ለህጎቿና ለስርዓቶቿ መገዛት እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡

ሁሉም ዜጎች  ለሚከተሉት ኃይማኖት ህግና ስርዓት ተገዥ በመሆን ለሀገር ሰላም አስተዋፅኦ እንዲያደርጉም ጥሪ ቀርቧል፡፡

(በህይወት አክሊሉ)