በህንድ ባለፈው ሳምንት ብቻ 260 ሺህ ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተገለጸ

መጋቢት 13/2013 (ዋልታ) – በህንድ ባለፈው ሳምንት ብቻ 260 ሺህ ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተገለጸ።
ይህም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በሳምንት የተመዘገበው ከፍተኛ አሃዝ መሆኑ ተገልጿል።
በወረርሽኙ እጅግ ከተጠቁ ግዛቶች መካከል ምዕራባዊው የማሃራሽትራ ግዛት ወደ 70 በመቶ የሚጠጋውን እንደምትይዝ የተገለጸ ሲሆን፣ ለወረርሽኙ መስፋፋት የበሽታው መከላከያ ዘዴዎችን በአግባቡ አለመተግበር መሆኑ ተነግሯል።
ለወረርሽኙ ስርጭት መስፋፋት አዲስ የተገኘው የኮቪድ-19 ዝርያ ሊሆን እንደሚችልም መላምት ተሰጥቷል።
በህንድ እስካሁን ድረስ ከ 11 ሚሊየን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፣ 160 ሺህ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ህይወታቸውን አጥተዋል።
በህንድ እ.አ.አ በ2021 የበሽታው ስርጭት የመቀነስ አዝማሚያ ቢታይበትም ባለፈው ሳምንት ግን በተቃራኒው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው በኮቪድ-19 መያዙን የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል።