ካርድ ለማውጣት ነገ አትበሉ፤ ነገ ከዛሬ ይጀምራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ሚያዚያ 06/2013 (ዋልታ) – “ካርድ ለማውጣት ነገ አትበሉ፤ ነገ ከዛሬ ይጀምራል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

6ኛው ብሔራዊ ምርጫ ሊከናወን ጥቂት ሳምንታት እንደቀሩት ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ዜጎች የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ይጠበቃል ብለዋል።

“የሕገ መንግሥታችን አንቀጽ 38 ሁሉም ኢትዮጵያዊ የመምረጥና የመመረጥ መብት እንዳለው ይደነግጋል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ “የሀገራችንን የነገ ዴሞክራሲ ለመወሰን፣ ዛሬ የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርድ እናውጣ። ካርድ ለማውጣት ነገ አትበሉ፤ ነገ ከዛሬ ይጀምራል” ሲሉ መራጮች የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ በምህበራዊ ትስስር ገፃቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የመራጮች ምዝገባ መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን፣ እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።