የዜግነት ግዴታን ለመወጣት እና ለመምረጥ መመዝገብ ያስፈልጋል – ጠ/ሚ ጽህፈት ቤት

ሚያዝያ 13/2013 (ዋልታ) – በንቃት የዜግነት ግዴታን ለመወጣት እና ለመምረጥ መመዝገብ እንደሚያስፈልግ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት አሳሰበ፡፡

መምረጥ ከዴሞክራሲያዊ መብቶች አንዱ መሆኑን የጠቆመው ጽህፈት ቤቱ፣ በመንግሥት ላይ ብቻ ሳይሆን በንቁ የዜጎች ተሳትፎ ላይ የተመሠረተ እና በሚገባ የሚተገበር ዴሞክራሲ እንዲኖር መመዝገብ አንደሚያስፈልግ አስታውቋል፡፡