የሰላም ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ ከሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል

ሚያዝያ 15/2013 (ዋልታ) – የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ ከሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ሳሚ ጃሚል አብዱላህ ጋር በስደት የሚገኙ ወገኖችን ወደ ሀገራቸው መመለስና በዘላቂነት ማቋቋም በሚቻልበት አግባብ ላይ ተወያይተዋል።

በውይይቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ የእህትማማችነት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በሚያስችሉ የትብብር መስኮች ላይ መክረዋል፡፡

እንዲሁም በዋነኝነት በስደት የሚገኙ ወገኖችን ወደ ሀገራቸው መመለስና በዘላቂነት ማቋቋም ላይ መወያየታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡