ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ጋር ተወያዩ

ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ
ሚያዝያ 15/2013 (ዋልታ) – የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ላይ የመከሩ ሲሆን፣ አምባሳደር አለልኝ ለዘመናት በታሪክ የሚገናኙትን ሀገራት ለማገልገል ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
አምባሳደሩ ከኢትዮጵያ ጋር በኢኮኖሚ፣ ፖለቲካና የፀጥታ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት መዘጋጀታቸውንም ገልጸዋል።
አምባሳደር አለልኝ አድማሱ የእስራኤል ፓርላማ አባል የነበሩ ሲሆን፣ በቅርቡ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ሆነው መሾማቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/waltainfo
የአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን
https://www.facebook.com/%D8%AA%D9%84%D9%81%D8%B2%D9%8A%D9%88%D9%86-%D9%88%D8%A7%D9%84%D8%AA%D8%A7-%D8%A8%D8%A7%D9%84%D8%B9%D8%B1%D8%A8%D9%8A-Walta-TV-Arabic-102134881551994/
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛው የትዊተር ገፃችን
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!