ዶ/ር ሙሉ ነጋ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው ተሾሙ

ዶ/ር ሙሉ ነጋ

ሚያዝያ 28/2013 (ዋልታ) – ዶ/ር ሙሉ ነጋ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው ተሾሙ፡፡

ተሾሙ፡፡

ከዚህ በፊት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት ዶ/ር ሙሉ ነጋ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው የተሾሙት ዶ/ር አብርሃም በላይ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ ነው፡፡

የአመራሮቹ ሹመት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሰጡ እንደሆነም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡