ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ጅቡቲ ገቡ

ግንቦት 06/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የልዑካን ቡድናቸው ዛሬ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ጅቡቲ ገብተዋል፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንዳመላከተው የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌህ በዓለ ሲመትን ለመታደምም ነው ወደ ጅቡቲ ያቀኑት፡፡