አራት የአየር መቆጣጠሪያ ታወሮች ነገ ይመረቃሉ

ግንቦት 06/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ አድርጎ ያስገነባቸው አራት የአየር መቆጣጠሪያ ታወሮች ነገ እንደሚመረቁ ተገለጸ፡፡
ታወሮቹ የተገነቡት በኦሮሚያ ክልል ባሌ ሮቤ ከተማ፣ በአማራ ክልል ኮምቦልቻ፣ በሲዳማ ክልል ሀዋሳ እና በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ መሆኑን ከባለስልጣኑ ማህበራዊ የትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡