የውሃ፣ የመስኖ እና የኢነርጂ ዘርፉ መሰረታዊ ፍላጎቶችን በማሟላት ላይ አተኩሯል – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

                    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ግንቦት 16/2013 (ዋልታ) – የውሃ፣ የመስኖ እና የኢነርጂ ዘርፉ ባለፉት 3 ዓመታት መሰረታዊ ፍላጎቶችን በማሟላት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ፡፡

ያለፉት ሦስት ዓመታት የውሃ፣ የመስኖ እና የኢነርጂ ዘርፍ የኢትዮጵያ ብልጽግና ራዕይ ዐበይት የስኬት ምዕራፎች መሰረታዊ ፍላጎቶችን በማሟላት እና ዜጎቻችን ክብራቸውን የጠበቀ ሕይወት እንዲኖሩ በማድረግ ላይ በትጋት መስራቱን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው የገለጹት፡፡