ሀራምቤ ዩኒቨርሲቲ 3683 ተማሪዎችን አስመረቀ

ሐምሌ 24/2013 (ዋልታ) – ሀራምቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ደረጃ ያሰለጠናቸውን 3683 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነዉ።

ለ18ኛ ዙር ተማሪዎችን በማስመረቅ ላይ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲዉ በ1995 ዓ.ም በቋንቋ እና በመምህራን ስልጠና ስራ የጀመረ ሲሆን ባሁኑ ጊዜ በቴክኒክ እና ሙያ በቀንና ማታ ፕሮግራም፣ በዲግሪ ፕሮግራም በቀን፣በማታና በርቀት ትምህርት እና በድህረ ምረቃ ፕሮግራም በማስተማር ላይ ይገኛል።

(በሶሬቻ ቀበኔቻ)