ሀገራችንን ለማዳን እንዘምታለን – የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ሠራተኞች

ነሃሴ 6/2013 (ዋልታ) – የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ሠራተኞች ሀገራችንን ለማዳን እንዘምታለን ሲሉ ቃል ገብተዋል።
ሠራተኞቹ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ለመደገፍ እና ሀገር ላይ የተቃጣውን ጦርነት ለመመከት ውሳኔ ላይ ደርሰዋል።
በሀገር ላይ የተቃጣውን ወረራ ለመመከት ሁሉም ዜጋ “ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ፥ የትም፣ መቼም፣ በምንም” በሚል መሪ ቃል ዘመቻ መጀመሩ ይታወቃል።
የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ሠራተኞችም ይህንኑ እውን ለማድረግ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለሀገር መከላከያ ድጋፍ ለማዋል፣ ደም ለመለገስ እና ስንቅ ለማዘጋጀት መስማማታቸውን ተገልጿል፡፡
ከሠራተኞቹ መካከልም ሀገራችን ስትወረር ተቀምጠን አናይም በማለት የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል ቃል የገቡ እንዳሉም ኦቢኤን ዘግቧል።