ሀገርን ከገጠማት ፈተና ለማላቀቅ የተመራቂ ተማሪዎች ሚና ከፋተኛ ሊሆን ይገባል – ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

ሐምሌ 9/2014 (ዋልታ) ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ባለፉት ሁለት አመታት ሀገሪቱ የገጠማት ችግር ከፍተኛ መሆኑን አንስተው ይህን ፈተና ለመሻገር የተመራቂ ተማሪዎች ሚና ከፍተኛ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

በርካታ ንፁሀን ዜጎች ለረሃብ ፣ ለጦርነት ፣ለመፈናቀል በአሳዛኝ ሁኔታ መዳረጋቸውን ያወሱት ፕሬዝዳንቷ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ዜጎች ህይወታቸውን ያጡበት ሁኔታ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያሳዘነ መሆኑን አብራርተዋል።

ተመራቂ ተማሪዎቹ ይህንና መሰል በሀገሪቱ የሚፈጠሩ ችግሮቾ እና እንግልቶችን በመረዳት የመፍትሔ እና የሰላም አጋር መሆን እንዳለባቸውም አንስተዋል፡፡

ተመራቂ ተማሪዎች ስራን ከመንግስት ብቻ ባለመጠበቅ ራሳቸውን ሥራ ፈጣሪ በማድረግ በግልና በቡድን በመደራጀት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል።

በግላቸው እና በቡድን ተደራጅተው ሥራ ፈጣሪ ለሚሆኑ ተማሪዎች መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍና የመስሪያ ቦታ እንደሚያመቻች አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ለተመራቂ ተማሪዎች እንዲሁም በከፍተኛ ጥረትና ትጋት ላስተማሯቸው ቤተሰቦቻቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

አመለወርቅ መኳንንት