ሀገር አቀፍ የሞዴል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ባዛር መካሄድ ጀመረ

ሚያዝያ 9/2014 (ዋልታ) ሀገር አቀፍ የሞዴል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ባዛር ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ንጉሡ ጥላሁን ጨምሮ የሚኒስቴሩ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ባዘጋጀው በዚህ ባዛር በመጀመሪያው ዙር 199 ተሳታፊዎችን እንደሚያስተናግድ የተነገረ ሲሆን ፤ 22 ሺሕ የመዲናዋ ነዋሪዎች ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህም የ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ገበያ ትስስር መፍጠር ያስችላል ነው የተባለው።

የ2014 በጀት ዓመት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አገር አቀፍ ኤግዝብሸንና ባዛር የመጀመሪያው ዙር ከሚያዚያ 9 እስከ15/2014 ዓ/ም እንዲሁም ሁለተኛው ዙር ከግንቦት 22 – 28/2014 ዓ.ም እንደሚካሄድ ነው የተገለፀው።

በሰለሞን በየነ