ሀገር ዐቀፉ የፌዴራልና የክልል መንግስታት የህግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ በሰመራ እየተካሄደ ነው

ታኅሣሥ 16/2014 (ዋልታ) ሀገር ዐቀፉ የፌዴራልና የክልል መንግስታት የህግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚመሩት መድረክ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መሆንን ጨምሮ የሁሉም ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች እና የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች ታድመውበታል።

መድረኩ ከዚህ በፊት በባሕር ዳር ተካሂዶ በነበረው የመጀመሪያው መድረክ አገሪቱ ባጋጠማት የኅልውና ዘመቻን አስመልክቶ የተቀመጡ አቅጣጫዎች አጠቃላይ አፈፃፀም እና አሁናዊ ሁኔታን ይገመግማል ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩ በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይም ውይይት ተደርጎ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡