ሁለቱ ሀገራት በማዕድንና ነዳጅ ዘርፍ በትብብር መስራት በሚችሉበት አግባብ ላይ ውይይት ተካሄደ

የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ

ሰኔ 6/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ በማዕድንና ነዳጅ ዘርፍ በትብብር መስራት በሚችሉበት አግባብ ላይ ውይይት ተካሄደ።

የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ ከኢኳቶሪያል ጊኒው አቻቸው ገብርኤል ምባጋ ጋር በአዲስ አበባ ውይይት ማድረጋቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

በውይይታቸውም ሀገራቱ በዘርፉ በትብብር ለመስራት ስምምነት መድረስ በሚችሉበት አግባብ ላይ ውይይት ማድረጋቸው ተጠቁሟል፡፡

የማዕድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ ሁለቱ ሀገራት በማዕድንና ነዳጅ ዘርፍ በትብብር መስራት የሚችሉበት አቅም እንዳላቸው ገልጸዋል።

በማዕድንና ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ እና በኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል የተመራ ልዑክ ባለፈው ሳምንት በኢኳቶሪያል ጊኒ ጉብኝት ማድረጉ ይታወሳል።

በወቅቱም በማዕድን እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ሀገራቱ በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW