ህወሓት ኤፍ-ኤች ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ ግብረሰናይ ድርጅትን መዝረፉ ተገለጸ

ነሀሴ 21/2021 (ዋልታ) – በደቡብ ጎንደር ዞን ላይ ጋይንት ወረዳ ነፋስ መውጫ ከተማ የዩኤስ አይ ዲ ቅርንጫፍ የሆነው ኤፍ-ኤች ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅት በአሸባሪው የትግራይ ቡድን መዘረፉ ተገለጸ፡፡

የኤፍ-ኤች ኢትዮጵያ የላይ ጋይንት ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አንተነህ አዳሙ እንዳሉት በአሸባሪው የትግራይ ቡድን የሠራተኞች መኖሪያ ቤትን ጨምሮ፣ የእህል መጋዘኖች፣ በርካታ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁስ ሙሉ በሙሉ ወድሟል።

የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች እና ጋራዥም ሙሉ በሙሉ ወድሟል ነው ያሉት።

መኪናን ጨምሮ 25 የፕሮጀክቱ የሞተር ሳይክሎች በህወሓት መዘረፋቸውን ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

አቶ አንተነህ ለአደጋ ጊዜና ለሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች አገልግሎት የሚውል 4ሺህ 551 ኩንታል በላይ እህል በአሸባሪው ቡድን መወሰዱንም አረጋግጠዋል።