ህዝባዊ የድጋፍ ሠልፍ በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል


ሐምሌ 15/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፋቸውን ለመግለጽና አሸባሪው ሕወሓትን ለመቃወም በመስቀል አደባባይ የሚያደርጉት ሰላማዊ ሰልፍ ተጀመረ፡፡
ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ህዝብ በላይ ከ11ዱ ክፍለ ከተማ በድጋፋ ሠልፍ ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል።
የድጋፍ ሠልፍ ህዝቡ ከመከላከያ ሠራዊት ጎን መቆሙን ለመግለፅ እና ሁለተኛ ዙር የህዳሴ ግድብ ሙሌት በሠላም መጠናቀቁ የፈጠረባቸውን የደስታ ስሜት ለማሳየት የሚደረግ መሆኑ ተመላክቷል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንደጀመርን ያለማንም ጣልቃ ገብነት እናጠናቅቀዋለን፣ የትግራይ ህዝብ አካላችን አሸባሪው ጁንታ ጠላታችን፣ የመከላከያ ሠራዊታችን የሉአላዊነታችን ምልክት ነው ኢትዮጵያ ታሸንፋለች የሚሉ እና ሌሎች ሀገራዊ ስሜትን የሚገልፁ መፈክሮችን በመያዝ ህዝቡ ድጋፋን በመግለፅ ላይ ይገኛል።
(በድልአብ ለማ)