ህዝብ ፀንቶ እንዲቆም ታሪኩን ማወቁ ወሳኝነት አለው – ዶ/ር እመቤት ሙሉጌታ

የካቲት 18 /2013 (ዋልታ) – ህዝብ ፀንቶ እና ጠንክሮ እንዲቆም ማንነቱን እና ታሪኩን ማወቁ ወሳኝነት እንዳለው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምክትል አካዳሚክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር እመቤት ሙሉጌታ ገለፁ።

125ኛው የአድዋ ድል በዓል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፓናል ውይይት እየተከበረ ይገኛል።

ዶ/ር እመቤት በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት በፓናል ውይይቶች የአድዋ ድል በዓልን ማክበር ድሉን ከመዘከር ባሻገር ታሪካችንን እንድናውቅ ያግዘናል ብለዋል።

የታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ በበኩላቸው የመጀመሪያው የአድዋ ድል በዓል ከድሉ ሰባት አመታት በኋላ እንደተከበረ እና በ1934 ዓ.ም በዓሉ ብሔራዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር በነጋሪት ጋዜጣ መደንገጉን አስታውሰዋል።

ውይይቱ ለሁለት ቀናት ቀጥሎ የሚካሄድ መሆኑም ታውቋል።

(በነስረዲን ኑሩ)