ህጻን ልጅን የኩላሊት ህመምተኛ በማስመሰል ሲለምኑ የተገኙ ግለሰቦች ተያዙ

ሚያዝያ 7/2014 (ዋልታ) ህጻን ልጅን የኩላሊት ህመምተኛ በማስመሰል ሲለምኑ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

የ10 ዓመት ህጻን ልጅን የኩላሊት ህመምተኛ በማስመሰልና በሀሰተኛ ሰነድ ገንዘብ ሲያሰባስቡ የተገኙ 11 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ጌታሁን አበራ ገልጸዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በ3 ክፍለ ከተሞች ስም የተዘጋጁ ሃሰተኛ ሰነድ እንዲሁም የሃኪም ማስረጃዎችን ከሚለምኑባቸው 2 ሚኒባስ መኪኖች ጋር በኅብረተሰቡ በተደረገ ጥቆማና በጸጥታ አካላት ክትትል በቁጥጥር ሥር ማዋል ተችሏል ብለዋል፡፡

በተደረገው የክትትል ሥራ ለህገ-ወጥ ስራው የተዘጋጁ ሃሰተኛ ሰነዶችን፣ ታርጋ ቁጥር 58456 እና 79169  ኮድ 3 ኦሮሚያ  ሚኒባስ ታክሲዎችን እንዲሁም 9 ሴትና 2 ወንዶች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።