‘ሆፕ ፕሮብ’ መንኮራኩር ወደ ማርስ የተሳካ ጉዞ አደረገች

ንብረትነቷ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የሆነችው ሆፕ ፕሮብ መንኮራኩር ወደ ማርስ የተሳካ ጉዞ አደረገች።

ማርስ ላይ በስኬት መድረስ የቻለችው ሆፕ ፕሮብ መንኮራኩርን ወደ ማርስ የመላክ ሂደት የጀመረው ከሰባት ወር በፊት ሲሆን በዛሬው ዕለት የማርስ ምህዋር ላይ ለመድረስ ችላለች።

የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ወደ ማርስ መንኮራኩር በመላክ ከአሜሪካ፣ ከቀድሞዋ ሶቪት ህብረት፣ ከአውሮፓ ህዋ ኤጀንሲና ከህንድ ቀጥሎ ከአለም አምስተኛዋ አገር መሆን የቻለች ሲሆን ከአረብ አገሮች ደግሞ ቀዳሚ አገር ለመሆን በቅታለች፡፡

ማርስ ላይ የማረፍን ተልዕኮ ለማሳካት የአገሪቱ የህዋ መሃንዲሶች በሼክ ማሃመድ ቢን ረሺድ ህዋ ማዕከል በመሆን ወደ ህዋ ከተጓዙ ጠፍርተኞች ጋር ግንኙነት በማድረግ መረጃ ሲለዋወጡ ቆይተዋል፡፡

የመንኮራኩሯ የጉዞ ሁኔታ በዛሬው ዕለት ወደ ማርስ ከመቃረቡ ጋር ተያይዞ በርካቶች በዱባይ ከሚገኘው ግዙፍ ከቡርጅ ሃሊፋ ህንጻ ስር በቀጥታ ስርጭት መከታተላቸውን ኢዜአ ዘግቧል።