ለመከላከያ ሰራዊት ከ78 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ

ኅዳር 24/2014 (ዋልታ) 2 ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ለአገር መከላከያ ሰራዊት ከ78 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።

ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ 45 ሚሊዮን ብር እንዲሁም አርሲ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ 30 ሚሊዮን ብርና 700 ኩንታል ጤፍ ድጋፍ አድርገዋል።

በተመሳሳይ የሰንሻይን መሪ ሉቄ መንደር ነዋሪዎች የልማት ማኅበር 2 ሚሊዮን እንዲሁም የአንበሳ ቢራ ፋብሪካ 1 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

ከተቋማቱ በተጨማሪ ማኅበራዊ የትስስር ገጽን ለበጎ ዓላማ በመጠቀም ወጣት አንተነህና ጓደኞቹ የተለያዩ የንፅህና መጠበቂያዎችን አሰባስበው ድጋፍ በማድረግ ለመከላከያ አጋርነታቸውን አሳይተዋል።

ድጋፉንም የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀው ለተቋማቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በትዕግስት ዘላለም