ለሰራዊቱ ከ37 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ተደረገ

መስከረም 13/2015 (ዋልታ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ለመከላከያ ሰራዊት ከካፋ ዞንና ምዕራብ ኦሞ ዞን ያሰባሰበውን የዓይነት ድጋፍ አስረከበ።

ክልሉ ለ2ኛ ጊዜ ከካፋ ዞን ህዝብ ያሰባሰበውን የ31 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ከምዕራብ ኦሞ ዞን ያሰባሰበውን ከ6 ሚሊየን በላይ የዓይነት ድጋፍ ነው በዛሬው ዕለት ያስረከበው።

ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ለሰራዊቱ ከሚደረገው ድጋፍ ጎን ለጎን የልማት ስራዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

የካፋ ዞን የመንግስት ተጠሪ አስረስ አስፋው በበኩላቸው ለመከላከያ ሰራዊት የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የምዕራብ ኦሞ ዞን አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኑሪ ኢብራሂም በዞኑ ለመከላከያ ሰራዊት ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ የአይነትና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።

በሱራፌል መንግስቴ