ለሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን አባላት የገንዘብና የመሬት ሽልማት ተበረከተ

የካቲት 2/2014 (ዋልታ) ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካን ዋንጫ ላነሳው የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን አባላት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል የገንዘብና የመሬት ሽልማት አበርክተዋል፡፡

ሴኔጋል ካሜሩን ባዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ፣ ግብጽን 4 ለ 2 በማሸነፍ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫ ማንሳቷ ይታወሳል፡፡