ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ17 ሺሕ ፓውንድ በላይ ድጋፍ ተደረገ

ጥቅምት 30/2014 (ዋልታ) – በኮቨንተሪ፣ በርሚንግሀም እና አካባቢው የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት በህወሃት ወረራ ከአካባቢያቸው ለተፈናቀሉ ኢትዮጵያዊያን ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ባካሄዱት የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር የተሰበሰበውን 17ሺህ 819 ፓውንድ ድጋፍ በዩናይትድ ኪን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ አስረክበዋል።

አምባሳደር ተፈሪ መለሰ በኮንቨንተሪ፣ ቤሪንግሀምና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በዚህ ወቅት ከህዝባቸውና ከመንግሥት ጎን በመቆም ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የሚያደርጉትን የገንዘብም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።