ለትግራይ ሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብ እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

ግንቦት 4/2014 (ዋልታ) – ለትግራይ ክልል ሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብ እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳምታዊ መግለጫው አስታወቀ፡፡
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በከፈተው የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማዕከል የመክፈቻ ሥነ ሥረዓት ላይ ለመገኘት ሐረማያ የሚገኙት የውጨ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው በሳምቱ ያከናወናቸውን ዐብይ ተግባራት ለጋዜጠኖች አብራርተዋል፡፡
በመግለጫው በሳምንቱ በፓለቲካ ዲፕሎማሲ መስክ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር የተሳካ ምክክር መደረጉ ጠቁመዋል፡፡
ከሰብአዊ እርዳታ ጋር በተያያዘ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል በአግባቡ እንዲደርስ መንግሥት የተቻለውን ሁሉ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
መንግሥት በትግራይ ያለው ችግር በሰላም እንዲፈታ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ቢሆንም አሸባሪው ሕወሓት ግን ፀብ አጫሪ ድርጊቱን እንዳላቆመ ለአሜሪካ አምባሳደር መግለጫ መሰጠቱንም ነው የገለፁት፡፡
በሳምንቱ በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ መስክም ከፍተኛ ሥራ እንደተሰራ አምባሳደሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ሱራፌል መንግስቴ (ከሐረማያ)