ለአረጋዊያን ክብር እንጓዛለን በሚል መሪ ሀሳብ የእግር ጉዞ በሀዋሳ እየተካሄደ ነው

ግንቦት 14/2014 (ዋልታ) በሀዋሳ “ለአረጋዊያን ክብር እንጓዛለን” በሚል መሪ ሀሳብ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተሳተፉበት የእግር ጉዞ በመካሄድ ላይ ነው ።

በመርሀ-ግብሩ ላይ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ስራ አስኬያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ፣ ታዋቂ አርቲስቶች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች፣ የመንግስት የሥራ ኃፊዎች፣ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

የእግር ጉዞው ዋና ዓላማ ትናንት ታሪክ የሰሩ አሁን ግን በብዙ ችግር ውስጥ የሚገኙ አቅመ ደካማ አረጋዊያንን በተቻለ ሁሉ የመደገፍ ባህልን ማዳበርና ተሳትፎ መጨመር ነው ተብሏል።

በሁሉም የእድሜ ክልል ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች በዚህ የእግር ጉዞ እየተሳተፉ እንደሚገኙ የኢዜአ ዘገባ አመላክቷል፡፡