ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምጣኔ ሃብት ትግበራ ውጤት

ነሐሴ 29/2013 (ዋልታ) በአየር ንብረት ለውጥ በማይበገር ምጣኔሃብት ትግበራ ስልት አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ገለፀ፡፡

ለዚህም ” የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር” ንቅናቄ አስተዋፅኦ እንዳደረገ ተመልክቷል፡፡

የአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን እና የተጠሪ ተቋማት የ2013 የበጀት ዓመት አፈፃፀም እና የ2014 ዕቅድ ውይይት ለ2 ቀናት በአዳማ እየተካሄደ ይገኛል።

ኮሚሽነሩ ፍቃዱ በየነ (ፕ/ር) የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ተግባራን ከአለፋት ዓመታት በላቀ መልኩ ለመተግበር እና ውጤታማ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በ2013 በየደረጃዉ ታቅደው በተለያዩ ምክንያቶች ተንጠባጥበው የቀሩትን ተግባራትን በዚህ ዓመት ዕቅድ በማካተት እንደሚሰራም ገልፀዋል፡፡

በሰለሞን በየነ