ለኢትዮጵያ ሆቴል የአትሌቲክስ ክለብ የስፖርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

የካቲት 21/2014 (ዋልታ) ሚስት ቡሽ ኢትዮጵያ ኮርፖሬሽን ለኢትዮጵያ ሆቴል የአትሌቲክስ ክለብ የስፖርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
ከተመሰረተ 10 ዓመታትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ሆቴል አትሌቲክስ ክለብ በአገሪቱ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ሚስት ቡሽ ኢትዮጵያም ክለቡን በመደገፍ በመጀመሪያ ዙር ለክለቡ አትሌቶች የትጥቅ ድጋፍ አድርጓል።
ክለቡ ዛሬ በሁለተኛ ዙር በተደረገ ድጋፍ የቤት ውስጥ መለማመጃ ማሽን እና የመሮጫ ጫማዎች ተበርክተውለታል።
በመሰረት ተስፋዬ