ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አቀባበል አየተደረገለት ነው

ሐምሌ 21/2014 (ዋልታ) በዓለም አትሌትክስ ሻምፒዮና አኩሪ ድል ላስመዘገበው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን፣ ቡድኑ ባረፈበት ስካይ ላይት ሆቴል በማርሽ ባንድ የታጀበ አቀባበል እየተደረገለት ነው፡፡

በአቀባበሉ ላይ የልዑካን ቡድኑ ቤተሰቦች፣ ክለቦችና ፌዴሬሽኖች ቡድኑ ባረፈበት ስካይ ላይት ሆቴል የአበባ ጉንጉን እያበረከቱ ይገኛሉ።

ቡድኑ ከዚህ መርኃ ግብር ቀጥሎ ካረፈበት ስካይላይት ሆቴል ተነስቶ በቅዱስ እስጢፋኖስ፣ 4 ኪሎ፣ ፒያሳ፣ ቸርችል አድርጎ በለገሀር ወደ መስቀል አደባባይ በመሄድ ደስታቸውን ከሕዝቡ ጋር የሚገልፁ ይሆናል።

በኦሪገን 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 10 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም 2ኛ ከአፍሪካ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቋ ይታወቃል፡፡

በሻምፒዮናው የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አባላት ትናንት ምሽት ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡