መጋቢት 9/2014 (ዋልታ) በሰርቢያ ቤልግሬድ ለ18ኛ ጊዜ የሚደረገው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በይፋ ተጀምሯል፡፡
ከደቂቃዎች በፊት በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር የማጣሪያ ውድድር የተካሄደ ሲሆን ኢትዮጵያን ወክለው በማጣሪያው የተሳተፉ 3ቱም አትሌቶች ውድድሩን በበላይነት በማጠናቀቅ ወደ ፍጻሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡
አክሱማይት እምባዬ በመጀመሪያው ምድብ 4:04.83 በሆነ ሰዓት በመግባት ቀዳሚ ሆና ለፍፃሜው ማለፏን አረጋግጣለች፡፡
በተመሳሳ ሂሩት መሸሻ በሁለተኛው ምድብ 4:05:67 በሆነ ሰዓት በመግባት ቀዳሚ ሆና ለፍፃሜው ስትቀርብ፤ በሶስተኛው ምድብ የተወዳደረችው ጉዳፍ ፀጋዬ ደግሞ 4:06:71 በሆነ ሰዓት በመግባት ቀዳሚ ሆና ለፍፃሜው ማለፏን አረጋግጣለች።
የፍፃሜ ውድድር ነገ የሚካሄድ ሲሆን ኢትዮጵያ በ3 አትሌቶች የምትወከል ይሆናል።
ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW