ሊጉ የፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ አደረገ

ግንቦት 8/2014 (ዋልታ) የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ የፕሮግራም እና መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል።

ሊጉ ጉባኤ ከማድረግ ባለፈ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ዝግጅት ማድረጉን ያስታወቀ ሲሆን የፕሮግራም እና የመተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ማድረጉንም ገልጿል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፕሬዝዳንት መሰረት መስቀሌ በሊጉ በቀጣይ ሦስት ወራት የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል እቅድ ተይዞ እየተሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የሊጉ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትም የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ውይይት ተደርጎ የአሰራር መመሪያ መፅደቁን አንስተዋል።

በቀጣይ ለሚካሄደው ጉባኤ ቅድመ ዝግጅት አቅጣጫ መቀመጡንም ጠቁመዋል።

በሱራፌል መንግሥቴ