“ልዩ ምልከታ” በሚል በወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ያደረገ መድረክ ተካሄደ

መጋቢት 22/2014 (ዋልታ) በኢትዮጵያ ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ያደረገ “ልዩ ምልከታ” የተሰኘ መድረክ ተካሄደ፡፡
በመድረኩ የመስኩ ባለሙያዎች፣ የመንግሥትን የሥራ ኃላፊዎች፣ የግሉ ዘርፍ አከናዋኞችን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
መድረኩ በብሩህ ማይንድስ ኮንሰለት የተዘጋጀ ሲሆን ”የሕግ እና የፖሊሲ ማዕቀፍ ለአንተርፕርነርሽፕ ዘርፍ ልማት ያለው ሚና በኢትዮጵያ” በሚል ሀሳብ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር እንዲሁም ከፌዴራል አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ኤጀንሲ የተወከሉ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት መድረክ በኢትዮጵያ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፖሊሲ አለመኖር ባስከተላቸው ችግሮች ዙሪያ፣ የሌሎች አገራት ተሞክሩ ያገናዘበ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
የወጣቶች ሥራ ፈጠራን ለማበረታታት ባለድርሻ አካላትን በቅርበት በማወያየት የፖሊሲ ግብዓት ለማቀበል፣ ተቋማዊ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ፣ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች በዲጂታል የቴክኖሎጂ ሥራዎቻቸውን በሚያበለፅጉበት እና የፋይናንስ ተደራሽት ሊስፋፉላቸው በሚችሉባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ መፍትሄ የሚያመላክት የውይይት መደረጉን ብሩህ ማይንድስ ኮንሰለት ለዋልታ ገልጿል፡፡
“ልዩ ምልከታ” የተሰኘው የውይይት መድረክ በየወሩ እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል፡፡