ሕወሓት ባደረሰው ውድመት ላይ የተሰራ ጥናት ይፋ ሊሆን ነው

መስከረም 25/2014 (ዋልታ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአሸባሪው ሕወሓት ቡድን በሰሜን ጎንደር ያደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ እያስጠና ያለውን ጥናት በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው የአሸባሪው ቡድን በሰሜን ጎንደር ያደረሰውን ውድመት እያስጠና ሲሆን፣ በጭናና ቦዛ አካባቢ አረመኒያዊ ድርጊት መፈጸሙን ገልጸዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ጥናት የደረሰውን ጉዳት በዝርዝር ለመለየትና ለተጎጂዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እንደሚያግዝ ተገልጿል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሰሜን ጎንደር የተለያዩ አካባቢዎች በባለሙያዎች ያስጠናውን ጥናት እያጠናቀቀ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

የዳሰሳ ጥናቱ የጥፋት ቡድኑ ግፍ በታሪክ ተፅፎ እንዲቀመጥና ትህነግን በአለም አቀፍ የጦር ወንጀል እስከማስጠየቅ ያለመ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በቦዛና ጭና አካባቢዎች ብቻ ትህነግ ከ200 በላይ ንፁሓን ዜጎችን መግደሉ የሚታወስ ነው፡፡