ሕጋዊ መንግሥትን ከአሽባሪ ቡድን ጋር እኩል የማየት ሴራ

መስከረም 11/2014 (ዋልታ)  ሕጋዊ መንግሥትን ከአሽባሪ ቡድን ጋር እኩል ማየት የሽብር ቡድኑን ጥቃት እንደ ጽድቅ መቁጠር ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሪታሪያት ቢልለኔ ስዩም ገለፁ፡፡

ይልቁንም ሰላምን ለማስፈን መንግሥታዊ ያልሆኑና አሸባሪ አካላትን ትጥቅ እንዲፈቱ እና የመንግሥት ተዋናዮች በሕገ መንግሥቱ የተሰጡትን ኃላፊነቶች እንዲወጡ ግፊት ማድረግን ይጠይቃል ሲሉ በቲዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ከዚህ ባሻገር ያለው አካሄድ ግን እንደማይጠቅምና ተገቢ እንዳልሆነ ነው ባስተላለፉት መልዕክት የገለፁት፡፡