መሐል ሜዳ፣ ጨፋ ሮቢት፣ ሐርቡና መኮይ ከተሞች ነጻ ወጡ

ኅዳር 24/2014 (ዋልታ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት በአሸባሪው ሕወሐት ተይዘው የነበሩትን መሐል ሜዳ፣ ጨፋ ሮቢት፣ ሐርቡና መኮይ ከተሞች ነጻ አውጥቷል።

ከየቦታው የተመታው አሸባሪው ኃይል ዘርፎና አውድሞ፣ መሣሪያውንም ይዞ እንዳይወጣ የየአካባቢው ሕዝብ ተደራጅቶ መንገድ በመዝጋት፣ የአሸባሪውን ጀሌዎች በመማረክ እምቢ ባሉትም ላይ ርምጃ በመውሰድ የሚጠበቅበትን ሁሉ እንዲያደርግ በዚሁ አጋጣሚ ዳግም ጥሪ ቀርቦለታል።