መሠረት ዳምጤ ጫንያለው የፌዴራል ዋና ኦዲተር ሆነው ተሾሙ

ሰኔ 2/2014 (ዋልታ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት 12ኛ መደበኛ ጉባዔው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀረቡለትን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር እና ምክትል ዋና ኦዲተር ሹመት በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።

በዚሁ መሰረት መሠረት ዳምጤ ጫንያለው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር፣ አበራ ታደሰ ኢቲቻ ደግሞ የመስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ኦዲተር ሆነው ተሹመዋል።

ተሿሚዎቹም በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ መፈፀማቸውን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW