ሚኒስቴሩ በወላይታ ዞን ለሚገኙ አቅመ ደካሞች ድጋፍ አደረገ


ሐምሌ 15/2013 (ዋልታ) –
የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር በወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ለሚገኙ ነዋሪዎች ድጋፍ አደረገ፡፡
ሚኒስቴሩ ለ30 አቅመ ደካሞች ምግብ ነክ ቁሳቁሶች፣ ለ80 ሴቶች የንጽህና መጠበቂያ፣ ለ100 ተማሪዎች የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች እንዲሁም የመኖሪያ ቤት እድሳት ለሚደረግላቸው 5 የዞኑ ነዋሪዎች የግንባታ ዕቃዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡
በተጨማሪም “ኑ ኢትዮጵያን እናልብስ” በሚለው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ያከናወነ ሲሆን ለዚህም ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉ ታውቋል፡፡
የሚኒስቴሩ አመራሮችና ሰራተኞች 5 ሺህ ችግኞችን ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን በጋራ ተክለዋል፡፡
(በሳሙኤል ሀጎስ)