ሚኒስቴሩ የአፍሪካ ህብረት ስብሰባን ለማካሄድ አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉን አስታወቀ

አምባሳደር መለስ ዓለም

የካቲት 7/2015 (ዋልታ) 36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤና 42ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባን ለማካሄድ አስፈላጊ ዝግጅት መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ የ51 አገራት ልኡክ ወደ አዲስ አበባ እንደሚገባም ተገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ጉባኤውን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት ማብራሪያ በጉባኤው የኢትዮጵያን ተሳትፎ ለማሳደግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በስብሰባው ኢትዮጵያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተመራ ልዑክ ትሳተፋለች ብለዋል።

36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤና 42ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ከየካቲት 8 እስከ 12 በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በመስከረም ቸርነት