ሚኒስቴሩ የ2015 የትምህርት ዘመን የፊታችን ሰኞ እንደሚጀመር ገለጸ

መስከረም 6/2015 (ዋልታ) በሀገር አቀፍ ደረጃ የ2015 የትምህርት ዘመን የፊታችን ሰኞ መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚጀመር ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በ2015 በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንደሚሆንም ተገልጿል።

ትምህረት ሚኒስቴር ከያዛቸው አዳዲስ አሠራሮችና ትግበራዎች መካከል ሥርዓተ ትምህርቱን ማሻሻል ዋነኛው እንደሆነ መጠቆሙን አሚኮ ዘግቧል።

ካሁን በፊት የነበረው ሥርዓተ ትምህርት አላስፈላጊ ነገሮቸ የታጨቁበት እና የይዘት ክፍተቶች ያሉበት መሆኑም ተነስቷል።

ሥርዓተ ትምህርቱ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎችን በማካተት ገለልተኛ በሆኑ አካላት እንደተዘጋጀ ተነግሯል።

የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ ትምህርትን በተመለከተ ከሆሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች በተመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሙከራ ትግበራ እንደሚጀመር ተገልጿል።