ሚኒስቴሮቹ በትምህርት ተቋማት ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎችን በጋራ ለመስራት ተስማሙ

መስከረም 20/2015 (ዋልታ) የትምህርት ሚኒስቴር እና ሰላም ሚኒስቴር በትምህርት ተቋማት ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎችን በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

የሁለቱን ተቋማት የጋራ ስምምነት የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም እና የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)ተፈራርመዋል።

የስምምነቱ ዋነኛ ዓላማ በትምህርት ተቋማት ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎችን በጋራ ለመስራት መሆኑ ኢዜአ ዘግቧል።

በሥነ ምግባር በማነፅ በሀገር ሰላም ግንባታ ላይ ትምህርት ቤቶች የበኩላቸው ሚና እንዲወጡ ለማድረግ መሆኑም ተመልክቷል።