ሚኒስትሩ ከውጪ የሚገቡ የግንባታ ግብዓቶችን በአገር ውስጥ በማምረት ለማስቀረት እንሰራለን አሉ

የማዕድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ

ጥር 9/2014 (ዋልታ) ከውጪ የሚገቡ የግንባታ ግብዓቶችን በአገር ውስጥ በማምረት ለማስቀረት እንሰራለን ሲሉ የማዕድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ በቢሾፍቱ የተገነባው ኢንዱስትሪ በቀጣይ ከውጪ የሚገቡ የግንባታ ግብዓቶችን ለማስቀረትና አገራዊ በሆኑ ምርቶች አቅማችንንና አገራዊ ፍላጎታችንን ለማሟላት ያስችለናል ብለዋል፡፡

የግሉ ክፍለ-ኢኮኖሚ ዘርፍ የማዕድን አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዲበራከቱ እንሰራለንም ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

የሴራሚክ ፋብሪካ ግንባታም ተጠናቆ ወደ ምርት እንዲገባ ከኦሮሚያ ክልል ባለድርሻ ተቋማት ጋር በቅንጅት ሠርተን ውጤቱን በጥቂት ወራት ውስጥ እናያለን ነው ያሉት፡፡

በሚኒስትሩ የተመራው ቡድን በቢሾፍቱ እየተገነባ ያለውን ሴራሚክ ፋብሪካ ጎብኝቷል፡፡