ሚኒስትሩ ወደ ትግራይ የሚሄደውን የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቀላጠፍ የሚደረገውን ጥረት ተመለከቱ

ግንቦት 27/2014 (ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ወደ ትግራይ ክልል የሚሄደውን የሰብአዊ ድጋፍ ለማቀላጠፍ የሚደረገውን ጥረት በአፋር ክልል ሰርዶ ኬላ ተገኝተው ተመልክተዋል።

መንግሥት ወደ ትግራይ ክልል የሚላኩ ሰብአዊ እርዳታዎች ለማሳለጥ እያደረገ ከሚገኘው ሁሉን ዐቀፍ ጥረት በተጓዳኝ አሸባሪው ሕወሓት ለጥፋት ዓላማው ሊጠቀምባቸው የሚችሉ ቁሳቁሶች እንዳይተላለፉ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የሰብአዊ እርዳታው በቀን እስከ 200 ኮንቦይ ተሽከርካሪ በሰርዶ ኬላ ተገቢው የፍተሻና ተያያዥ ቁጥጥር ከተደረገበት በኋላ አንደሚላክ በጉብኝታቸው መረዳታቸውን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በጉብኝቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እንዲሁም ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።