ባለስልጣኑ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ሰባት ሚሊየን ብር ደገፈ

ሚያዝያ 25/2014 (ዋልታ) የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሰባት ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ባለስልጣኑ ለሀገር እድገት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

በክልሉ ያጋጠመውን የድርቅ አደጋ ለመቋቋም ያስችል ዘንድ ባልስልጣኑ ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

እስካሁን እንደ አገር ለገጠሙ ተግዳሮቶች ባለስልጣኑ የመፍትሔ አካል በመሆን በርካታ ሥራ መስራቱ የተገለፀ ሲሆን በአማራ እና አፋር ክልል በጦርነቱ ምክንት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ተነግሯል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ያጋጠመውን የድርቅ አደጋ ተከትሎም ከተለያዩ አካላት እስካሁን የአራት ቢሊየን ብር ግምት ያላቸው የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገልጸዋል::

እንዲሁም ሀገር ለሚያጋጥማት ሰው ሰራሽም ይሁን ተፈጥሯዊ አደጋዎች መቋቋም የሚያስችል አቅምን መፍጠር ያሻል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም እንደ ኦሮሚያ ክልል “ጎሳ ጎኖፋ” የተሰኘ ማኅበር መቋቋሙን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የተከሰተውን የድርቅ አደጋ ለመቋቋምም በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በሔብሮን ዋልታው

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW